ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት።
2 ሳሙኤል 17:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መተኛ ምንጣፎች፥ ወጭቶችና የሸክላ ዕቃዎች ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ስንዴና ገብስ፥ ዱቄትና የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላና ምስር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መተኛ ምንጣፎች፣ ወጭቶችና የሸክላ ዕቃዎች ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ስንዴና ገብስ፣ ዱቄትና የተጠበሰ እሸት፣ ባቄላና ምስር፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ምንቸቶችንና የሸክላ ማሰሮዎችን፥ የመኝታ አልጋዎችንም ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ለዳዊትና ለተከታዮቹ የሚሆን ስንዴ፥ ገብስ፥ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ አተር፥ ማር፥ አይብ፥ እርጎና በጎችን አመጡ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ዳዊትና ተከታዮቹ በበረሓ ኑሮ እንደሚርባቸው፥ እንደሚጠማቸውና እንደሚደክማቸው በማሰብ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር አልጋዎችና ምንጣፎች፥ ዐሥርም ጋኖችና ፊቀኖች፥ የስንዴና የገብስ ዱቄት፥ ስልቅ አተርና ምስር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቦአል፥ ደክሞአል፥ ተጠምቶአል ብለው ምንጣፍ፥ ዳካ፥ የሸክላም ዕቃ፥ ይበሉም ዘንድ |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት።
በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።
አቢጌልም ጊዜ አላጠፋችም፤ ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት አቁማዳ የወይን ጠጅ፥ አምስት የተሰናዱ በጎች፥ አምስት መስፈሪያ የተጠበሰ እሸት፥ መቶ የወይን ዘለላና ዘቢብ፥ ሁለት መቶ ጥፍጥፍ የበለስ ፍሬ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።