ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
2 ሳሙኤል 13:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ወንድም የሻምዓ ልጅ ዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “የተገደሉት የንጉሡ ልጆች በሙሉ እንደ ሆኑ አድርጎ ጌታዬ አያስብ፤ የሞተው አምኖን ብቻ ነው። አምኖን እኅቱን ትዕማርን በግድ ከደፈራት ጊዜ አንሥቶ አቤሴሎም ይህን ጉዳይ ቆርጦ የተነሣበት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “የንጉሡን ልጆች በሙሉ እንደ ፈጇቸው አድርጎ ጌታዬ አያስብ፤ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጊዜ አንሥቶ አቤሴሎም ቈርጦ የተነሣበት ጕዳይ ስለ ሆነ፣ የሞተው አምኖን ብቻ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ዮናዳብ ግን እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ! የተገደሉት ልዑላኑ በሙሉ አይደሉም፤ የተገደለው አምኖን ብቻ ነው፤ አቤሴሎም ይህን ለማድረግ ያቀደው አምኖን የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና ከደፈረበት ጊዜ አንሥቶ እንደ ነበር ፊቱን አይተህ መረዳት ትችላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ መልሶ እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ጐልማሶቹ የንጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያስብ፤ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጀምሮ በአቤሴሎም ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረና የሞተ አምኖን ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ፦ ጌታዬ ጕልማሶቹ የንጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያስብ፥ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጀምሮ በአቤሴሎም ዘንድ የተቆረጠ ነገር ነበረና የሞተ አምኖን ብቻ ነው። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”