2 ሳሙኤል 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሟ አቤሴሎምም፥ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበርን? እኅቴ ሆይ፥ በይ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለሆነ፥ ነገሩን በልብሽ አትያዠው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድምዋ አቤሴሎም ባያት ጊዜ “እኅቴ ሆይ! ወንድምሽ አምኖን አስነወረሽን? እባክሽ እንደዚህ አትበሳጪ፤ እርሱ ወንድምሽ ስለ ሆነ ለማንም አትናገሪ” አላት። ስለዚህ ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ከሰው የተለየች ብቸኛ ሆና ተቀመጠች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምዋም አቤሴሎም፥ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትናገሪ ዘንድ በልብሽ አታስቢ” አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት መበለት ሆና ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምዋም አቤሴሎም፦ ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፥ ወንድምሽ ነው፥ ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች። |
ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው።