2 ሳሙኤል 13:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ ጌጠኛ የሆነና በዚያ ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን ዐይነት ልብስ ለብሳ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕማርም የአምኖን አሽከር ከቤት አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ዘመን ያላገቡ የነገሥታት ልጆች ይለብሱት የነበረውን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር፤ እርስዋም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳ እጅዋን በራስዋ ላይ በመጫን ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ እንዲህ ያለውን ልብስ ይለብሱ ነበርና፤ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና፥ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት። |
“ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጉርጉር ልብስ።”