2 ሳሙኤል 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀዳድዔዜር መልክተኞችን ሰዶ ከወንዙ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጣ፤ እነርሱም በሀዳድዔዜር ሠራዊት አዛዥ በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አድርአዛር መልክተኞችን ሰድዶ ከወንዙ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጣ፤ እነርሱም በአድርአዛር ሰራዊት አዛዥ በሶባክ መሪነት ወደ ኤላም ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጾባው ሀዳድዔዜር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኙት ሶርያውያን መልእክት ላከ፤ እነርሱም የሀዳድዔዜር የሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አድርአዛርም ልኮ በካላማቅ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን ሰበሰባቸው፤ ወደ ኤላምም መጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶቤቅ በፊታቸው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አድርአዛርም ልኮ በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አመጣ፥ ወደ ኤላምም መጡ፥ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶባክ በፊታቸው ነበረ። |
ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤
እንደገናም ጌታ ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥
ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ መልእክተኞች ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ።