1 ዜና መዋዕል 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ መልእክተኞች ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፣ መልእክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጡ፤ እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ሰራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ከኤፍራጥስ በስተ ምሥራቅ በኩል ካሉት የሶርያ ግዛቶች ሠራዊት አስመጥተው በሾባክ አዛዥነት ሥር አደረጉአቸው፤ ሾባክ የጾባ ንጉሥ የሀዳድዔዜር የጦር አዛዥ ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሶርያውያንም እስራኤል ድል እንዳደረጓቸው ባዩ ጊዜ መልእክተኞችን ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶፋክ በፊታቸው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ መልእክተኞች ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |