2 ጴጥሮስ 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” እንዲሁም “እርያ ብትታጠብ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል” እንዲሁም “ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የተፋውን ለመዋጥ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል።” እንዲሁም “ዐሣማ ከታጠበ በኋላ ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” ደግሞ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፦ የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። |