ከእኛ አቅራቢያ ነገሥታትና የመንግሥታችን ጐረቤቶች ምቹ ጊዜ አግኝተናል ብለው እንዲያስቡና እንዳይጠብቁ ወደ ላይኛው ሀገር በፍጥነት በሄድኩበት ጊዜ ከእናንተ ለብዙዎቹ አደራ ብሎ የሰጠኋችሁን ልጄን አንጥዮኩስን ንጉሥ እንዲሆን ወስኛለሁ፤ ደብዳቤም እንዲህ ብዬ ጽፌለታለሁ፤