በባቢሎን አገር በገላትያ ሰዎች ላይ በተደረገው ጦርነት ላይ ተካፋዮች የነበሩ ሰዎች ቁጥራቸው በአራት ሺህ መቄዶያናውያን ሌላ ስምንት ሺህ አይሁዳውያን ነበሩ፤ የመቄዶንያ ሰዎች ጦር ወደ ኋላ ባለ ጊዜ ስምንቱ ሺህ አይሁዳውያን መቶ ሃያ ሺህ ጠላቶች ደምስሰዋል፤ ይህንን ማድረግ የቻሉት ከእግዚአብሐር በተደረገላቸው እርዳታ ነው፤ ብዙ ምርኮም አግኝተዋል”።