ይሁዳ መቃቢስና ጓደኞቹ በሥውር ወደ መንደሮች ገቡ፤ የአገራቸውንም ሰዎች ጠሩ፤ በአይሁዳቹ ሕግ ተጠብቀው የኖሩትን ወደ እነርሱ አምጥተው ስድስት ሺህ የሚያህሉ ሰዎችን ሰበሰቡ።