እኔም እንደ ወንድሞቼ ስለ አባቶቼ ሕግ ሥጋዬንና ሕይወቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር ለሕዝባችን ቶሎ እንዲራራና አንተንም በፈተናና በመቅሠፍት እርሱ ብቻ አምላክ መሆኑን ለማወቅ እንዲያስችልህ እለምነዋለሁ፤