የእርሱ ወታደሮች የምሽጉን ግንብ ለመያዝና የውጪውን በር ለማፈረስ በመታገል ላይ ነበሩ፤ መዝጊያዎችንም ለማቃጠል ታዘው ነበረ። ራዝያስ በሁሉም ቦታ ስለተከበበ የገዛ ራሱን በሰይፍ ወጋ፤