ይሁዳ መቃቢስም በበኩሉ ከኒቃኖር ጋር ያለው ግንኙነት እየቀዘቀዘ መሄድንና ሲገናኘውም ቁጣ ቁጣ የሚለውም መሆኑን በመገንዘብ ይህ ነገር መልካም አለመሆኑን አሰበ። ስለዚህ ከሰዎቹ ብዙዎቹን ሰበሰበና ይዞ ከኒቃኖር ተሠወረ።