ነገር ግን የነገሥታት ንጉሥ የሆነው አምላክ በዚህ በእርጉም ሰው ላይ የአንጥዮኩስን ቁጣ አስነሣበት፤ መነላዎስን የክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያት መሆኑን ሊስያስ ለንጉሡ ባስረዳ ጊዜ ነጉሡ ወደ ቤሪያ እንዲወስዱትና እንደ ሀገሩ ልማድ እንዲገድሉት አዘዘ።