ይሲጦስ ከባኬኖር (ከጦብ) ሰዎች አንድ ጀግና ፈረሰኛ የሆነው ሰው ጐርጊያስን በልብሱ ይዞ ይህን እርጉም ሰው ለመማረክ ይጐትተው ነበር፤ ነገር ግን አንድ የትራኪስ አገር ፈረሰኛ ወደ ይሲጦስ ሮጠና ትከሻውን በሰይፍ መታው፤ ጐርጊያስም አመለጠና ወደ ማሬሳ ሸሸ።