ጠላቶቹን ካሸነፈና ካጠፋ በኋላ ጦር ሠራዊቱን ወደ ኤፍሮን አዘመተ፤ ኤፍሮን ሊስያስ የሚኖርባት ምሽግ ከተማ ናት፤ እዚያ ጠንካራ ወጣቶች ከግንቡ ፊት ለፊት ቦታቸውን ይዘው በጥንካሬ ይዋጉ ነበር፤ በክልሉም ብዙ የጦር መሳሪያዎች ተምዘግዛጊዎች ነበሩ።