ጢሞቴዋስም በጰሲጦስና በሱሊጳጥሮስ ወታደሮች እጅ ወደቀ፤ እንዳይገሉትና እንዲለቁት ለመናቸው፥ “ዘመዶቻችሁና ከወንድሞቻችሁ አብዛኞቹ በእኔ ሥልጣን ሥር ያሉ ናቸው፤ በእኔ ሞት ምክንያት እነርሱ ጉዳት እንዳይደርስባቸው” ሲል እንዲለቁት በተንኮል ተናገራቸው።