እነዚህን ሥርዓቶች ከፈጸሙ በኋላ በግምባራቸው ተደፍተው፤ እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት መቅሰፍት ላይ እንዳይጥላቸው፥ ኃጢአት ላይ ቢወድቁም በመጠኑ እንዲያርማቸው (እንዲቀጣቸው) እንጂ ከተሳዳቢዎችና ከጨካኞች አረማውያን እጅ እንዳይጥላቸው ለመኑት።