ሌሎችም በዚሁ ዓይነት በግንቡ ውስጥ ወደነበሩት ሰዎች በሌላ በኩል ገብተው ግንቦቹን አቃጠሉ፤ እሳት አንድደውም ተሳዳቢዎቹን በሕይወታቸው እያሉ አቃጠሉዋቸው። የፊተኞቹ ወታደሮች መዝጊያዎቹን ሰባበሩና የቀረውን ጦር ሠራዊት አስገቡ፤ ከተማዋን ለመያዝም የመጀመሪያዎቹ ሆኑ።