በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፥ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
2 ነገሥት 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነገሠም ጊዜ የሀያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች። እርሷም የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነገሠም ጊዜ የኻያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገሥም በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ ልጅ ነበረች። |
በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፥ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
በዚህ ዓይነት አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መኖሪያውን በቲርጻ አድርጎ ነበር።
አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች።