ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።”
2 ነገሥት 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ የከተማይቱ ቅጽር በር የቅርብ ባለሟሉ በሆነው አገልጋዩ ኀላፊነት ሥር እንዲጠበቅ አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ያንን አገልጋይ ሕዝቡ ስለ ረጋገጠው በዚያ ሞተ፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ኤልሳዕን ለማነጋገር በሄደ ጊዜ ኤልሳዕ በዚያ አገልጋይ ላይ የተናገረበት የትንቢት ቃል ስለ ተፈጸመ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ንጉሡ እጁን ይደግፈው የነበረውን የጦር አለቃ፣ የቅጥሩ በር ኀላፊ አድርጎት ነበርና በበራፉ መተላለፊያ ላይ ሕዝቡ ሲጋፋ ረጋገጠው፤ ያ የእግዚአብሔር ሰው ንጉሡ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አስቀድሞ እንደ ተናገረውም የጦር አለቃው ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ የከተማይቱ ቅጽር በር የቅርብ ባለሟሉ በሆነው አገልጋዩ ኀላፊነት ሥር እንዲጠበቅ አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ያንን አገልጋይ ሕዝቡ ስለ ረጋገጠው በዚያ ሞተ፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ኤልሳዕን ለማነጋገር በሄደ ጊዜ ኤልሳዕ በዚያ አገልጋይ ላይ የተናገረበት የትንቢት ቃል ስለ ተፈጸመ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ያን እጁን ይደግፈው የነበረውን ብላቴና በሩን ይጠብቅ ዘንድ አቆመው። ሕዝቡም በበሩ ረገጠው፥ መልእክተኛው ወደ እርሱ በወረደ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረውም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ያን እጁን ይደግፈው የነበረውን አለቃ በሩን ይጠብቅ ዘንድ አቆመው። ሕዝቡም በበሩ ረገጠው፤ ንጉሡም ወደ እርሱ በወረደ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው ሞተ። |
ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።”
ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?