2 ነገሥት 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ሸለቆው ግን በውሃ ይሞላል፤ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና ሌሎች እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም፥ ከብቶቻችሁም፥ እንስሶቻችሁም፥ ትጠጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውሃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’ |
እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።