2 ነገሥት 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘በባዕድ አገር ጉድጓድ ቆፍሬ፥ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ’ ብለህ ታብየሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባዕድ ምድር የውሃ ጕድጓዶችን ቈፈርሁ፤ በዚያም ውሃ ጠጣሁ። የግብጽን ምንጮች ሁሉ፣ በእግሬ ረግጬ አደረቅሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በባዕድ አገር ጒድጓድ ቆፍሬ፥ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ’ ብለህ ታብየሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕረፍት አደረግሁ፤ የባዕድ ውኃንም ጠጣሁ፥ የተገደበውንም ውኃ ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቈፈርሁም፤ እንግዳውንም ውሃ ጠጣሁ፤ የተገደበውንም ውሃ ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ፤” ብለህ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ። |
ቤንሀዳድም “በሰማርያ ለያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ!” ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት።