2 ነገሥት 12:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አደሙበት፤ ከእነርሱም ሁለቱ የሺምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ይሆዛባድ ወደ ሲላ በሚወስደው ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በተደለደለ መሬት ላይ በተሠራው ቤት ገደሉት፤ ኢዮአስም በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮቹም ተነሥተው ዐመፁበት፥ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በመሀሎ ቤት ኢዮአስን ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
ኢዮርብዓም ለዐመፅ የተነሣሣበትም ታሪክ እንደሚከተለው ነው፥ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጽሮች እየጠገነ በማደስ ላይ ነበር።
አሜስያስም ጌታን ከመከተል ከራቀ በኋላ በኢየሩሳሌም ሤራን አሤሩበት፥ ወደ ለኪሶም ኰበለለ፤ ከኋላውም የሚከታተሉትን ሰዎች ወደ ለኪሶ ላኩበት፥ በዚያም ገደሉት።