2 ቆሮንቶስ 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሁለተኛ ጊዜ ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እንደነገርኳችሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ እንደገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ለሠሩት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ እናገራለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ጕብኝቴ እናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፤ አሁንም በሩቅ ሆኜ እንደ ገና አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ወደ እናንተም ተመልሼ ስመጣ፣ ከዚህ በፊት ኀጢአት ለሠሩትም ሆነ ለሌሎች አልራራላቸውም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለተኛው ጒብኝቴ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ በማስጠንቀቅ ተናግሬ ነበር፤ አሁንም ደግሞ በሩቅ ሆኜ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ለሠሩትና ለሌሎችም በማስጠንቀቅ እናገራለሁ፤ አሁን ወደ እናንተ ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ለማንም አልራራም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቱን አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ አሁንም አስቀድሜ እናገራለሁ፤ ቀድሞ ከእናንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገርሁአችሁ፥ አስቀድሞ ለበደሉ፥ ለሌሎችም ሁሉ እንደ ገና የመጣሁ እንደ ሆነ ርኅራኄ እንዳላደርግ፥ እንዲሁ ሳልኖር ለሦስተኛ ጊዜ እናገራለሁ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው። |
እነሆ፥ ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ ያላችሁን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ ሊያከማቹ አይገባቸውምና።
ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።