2 ዜና መዋዕል 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ዮዳሄ በጌታ ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ዮዳሄ በአምላክ ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮች፣ ትላልቅና ትናንሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተጠብቀው ይኖሩ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለጦር መኰንኖች ሰጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ኢዮአዳ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ሰይፍና ጦር፥ አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። |
ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ እየያዘ በንጉሡ ዙሪያ ከቤቱ ቀኝ እስከ ቤቱ ግራ ድረስ በመሠዊያውና በቤቱ አጠገብ እንዲቆም አደረገ።
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ዮዳሄ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ በሰንበት ቀን ይገቡ የነበሩትን በሰንበትም ቀን ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል፥ እነሆ፥ ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።