1 ሳሙኤል 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥ “የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለራእዩ ቤት የት እንደ ሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም በቅጽሩ በር አጠገብ ወደነበረው ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፥ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፦ የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለው። |
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ፤ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጠዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ።