1 ሳሙኤል 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከዔቅሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ወርዶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጋት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን የያዙአቸው በዔቅሮንና በጋት መካከል የነበሩትም ከተሞች ሁሉ ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያንም ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳኑ፤ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ዕርቀ ሰላም ወርዶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ፤ ጌት ድረስ ከእስራኤል ልጆች የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፤ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰዱ። በእስራኤልና በአሞራውያን መካከልም ሰላም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ ጌት ድረስ ከእስራኤል የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፥ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳነ። በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ዕርቅ ነበረ። |
በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።”
ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የዔግሎም ንጉሥ፥ እነርሱና ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ በገባዖንም ዙርያ ሰፈሩ በእርሷም ላይ ጦርነት አደረጉ።
ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
በሐጾር ንጉሥ በየቡስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ሮጠ።