1 ሳሙኤል 31:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፤ ቀስተኞችም አገኙት፥ በቀስታቸውም ወግተው ክፉኛ አቆሰሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፤ ቀስተኞችም ደርሰው ክፉኛ አቈሰሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጦርነቱ በሳኦል ዙሪያ ስለ በረታ ቀስተኞች ሳኦልን አገኙት፤ ወግተውም በጣም አቈሰሉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፤ ቀስተኞችም አገኙት፤ ታፋውንም ወጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፥ ቀስተኞችም አገኙት፥ እርሱም ከቀስተኞቹ የተነሣ እጅግ ተጨነቀ። |
ዳዊትም፥ “እስቲ ምን ነገር እንደተፈጠረ ንገረኝ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነቱ ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል፤ ሞተዋልም፤ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ሳለ፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከትለው ደረሱበት፤
ዳዊት ሄዶ፥ ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤት ሻን አደባባይ ከሰረቁት ከያቤሽ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥
ይሁን እንጂ በአጋጣሚ አንድ የሶርያ ወታደር ፍላጻ በማስፈንጠር ንጉሥ አክዓብን በጦር ልብሱ መገናኛ ላይ መታው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን “እኔ ቆስያለሁ! ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ!” ሲል አዘዘው።