1 ሳሙኤል 31:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አጥንቶቻቸውንም በከተማው ውስጥ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ቀብረው ሰባት ቀን ጾሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አጥንቶቻቸውንም ወሰዱ፤ በኢያቢስም ባለው የእርሻ ቦታ ቀበሩአቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥንታቸውንም ወሰዱ በኢያቢስም ባለው በአጣጡ ዛፍ በታች ቀበሩት፥ ሰባት ቀንም ጾሙ። |
ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።