1 ሳሙኤል 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ሳኦልም፣ ዳዊትና ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፣ በጊብዓ ኰረብታ ላይ በአጣጥ ዛፍ ሥር፣ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ ሹማምቱም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ያሉበት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦልም በራማ በሚገኘው በመሰማርያው ቦታ በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላቴኖቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንደ ተገለጡ ሰማ። ሳኦልም በጊብዓ በአጣጥ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፥ ባሪያዎቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |