1 ሳሙኤል 30:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶቹን፥ በዚያ የነበሩትን ወጣቶችና ሽማግሌዎቹን ሁሉ ማርከው ወሰዱ፤ የማረኩትንም ይዘው ከመሄድ በስተቀር አንዱንም አልገደሉም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቶቹን፣ በዚያ የነበሩትን ወጣቶችና ሽማግሌዎቹን ሁሉ ማርከው ወሰዱ፤ የማረኩትንም ይዘው ከመሄድ በቀር አንዱንም አልገደሉም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶችንና በውስጡም የነበሩትን ሁሉ ማርከው ወስደዋል፤ ከዚያም ለቀው ሲሄዱ ያገኙትን ሁሉ ማርከው ወሰዱ እንጂ ማንንም አልገደሉም ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶቹንና በውስጥዋም የነበሩትን ሁሉ ከታናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማርከው ነበር፤ ሁሉንም ወስደው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን አልገደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶቹንና በውስጥዋም የነበሩትን ሁሉ ከታናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማርከው ነበር፥ ሁሉንም ወስደው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንድስ እንኳ አልገደሉም ነበር። |
ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።
ትንሽም ሆነ ትልቅ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ሆነ ሌላ፥ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም። ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ።