1 ሳሙኤል 30:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትንሽም ሆነ ትልቅ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ሆነ ሌላ፥ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም። ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፣ ምርኮም ሆነ ሌላ፣ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም፤ ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድም የጐደለ ሳይኖር ዳዊት የተከታዮቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ እንዲሁም ዐማሌቃውያን ማርከው የወሰዱትን ምርኮ ሁሉ አስመለሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ፥ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የተወላቸው የለም፤ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የጎደለባቸው የለም፥ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ። |
እንዲሁም ዳዊት የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ፤ ሰዎቹም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” እያሉ መንጋውን ከሌሎች ከብቶች ፊት ለፊት ይነዱ ነበር።
ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።