1 ሳሙኤል 30:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብፃዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት። የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብጻዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት፤ የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ግብጻዊ ወጣት ከበረሓ ሲመጣ አግኝተው ወደ ዳዊት አቀረቡት፤ እነርሱም የሚመገበው እህል ሰጥተውት በላ፤ ውሃም አጠጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበረሃውም ውስጥ አንድ ግብፃዊ አግኝተው ወደ ዳዊት ይዘውት መጡ፤ እንጀራም ሰጡትና በላ፤ ውኃም አጠጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበረሀውም ውስጥ አንድ ግብጻዊ አግኝተው ወደ ዳዊት ይዘውት መጡ፥ እንጀራም ሰጡትና በላ፥ ውኃም አጠጡት፥ |
እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቁራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፥ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።