1 ሳሙኤል 30:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በደቡብ አገርና በጺቅላግ ላይ ዘምተው ነበር፥ ጺቅላግንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥ |
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ የተቀደደ ልብስ የለበሰ፥ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት መጥቶም በግምባሩ በመደፋት እጅ ነሣ።
አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።
ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።”
የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአኪሽ ላይ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው እንዲመለስ አድርግ፤ ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን ከእኛ ጋር አይወርድም። እዚህ ያሉትን የእኛን ሰዎች ራስ ቆርጦ ካልወሰደ በስተቀር፥ ከጌታው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል?