Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 12:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንደ እግዚአብሔርም ሠራዊት ታላቅ ሠራዊት እስኪሆን ድረስ ዳዊትን ለመርዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፣ ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጐርፉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በየቀኑ አዳዲስ ሰዎች ወደ ዳዊት ሠራዊት እየመጡ ይቀላቀሉ ስለ ነበር ብዙ ሳይቈይ የዳዊት ሠራዊት እጅግ የበዛና ኀያል ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት ታላቅ ሠራ​ዊት እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንደ እግዚአብሔርም ሠራዊት ታላቅ ሠራዊት እስኪሆን ድረስ ዳዊትን ለመርዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 12:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው!” አለ። የዚያንም ስፍራ ስም ማሃናይም ብሎ ጠራው።


በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር።


ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።


መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት።


እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።


እርሱም፦ “አይደለሁም፤ እኔ የጌታ ሠራዊት አዣዥ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ “ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድነው?” አለው።


አሁንም አብረውህ ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማለዳ ተነሡ፤ በጥዋት ፀሐይ እንደ ወጣችም ሂዱ” አለው።


በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች