ነገር ግን የሚመካው፦ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ ጌታ መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ ነገሮች እነዚህ ናቸውና፥ ይላል ጌታ።”
1 ሳሙኤል 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ጊዜ ሳሙኤል ጌታን ገና አላወቀም ነበር፤ የጌታም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ጊዜ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ከዚያ በፊት እግዚአብሔር ተናግሮት ስለማያውቅ የእግዚአብሔር ድምፅ መሆኑን አላወቀም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤል ግን ከዚህ በፊት ገና እግዚአብሔርን አላወቀም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ አልጠራሁህም፥ ተመልሰህ ተኛ ብሎ መለሰ። ሳሙኤል ግን ገና እግዚአብሔርን አላወቀም ነበረ፥ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር። |
ነገር ግን የሚመካው፦ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ ጌታ መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ ነገሮች እነዚህ ናቸውና፥ ይላል ጌታ።”
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላስል ነበር። ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ።
ደግሞም እግዚአብሔር፥ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም ግን፥ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው።
ጌታም ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም በዚህ ጊዜ ሳሙኤልን ይጠራ የነበረው ጌታ መሆኑን ተረዳ።