1 ቆሮንቶስ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላስል ነበር። ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሕፃን በነበርኩ ጊዜ እንደ ሕፃን እናገር ነበር፤ እንደ ሕፃን አስብ ነበር፤ እንደ ሕፃን እመራመር ነበር፤ ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የሕፃንነቴን ጠባይ ተውኩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እኔ ልጅ በነበርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመክር ነበር፤ በአደግሁ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቍኦጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |