1 ሳሙኤል 29:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ለአኪሽ፥ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፥ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፥ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ስለ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም አንኩስን፣ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፣ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፣ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋራ የማልዋጋው ስለ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ጌታዬ ምን በደል ሠራሁ? አንተን ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ በደል ካልተገኘብኝ ጌታዬና ንጉሤ የሆንከውን አንተን ተከትዬ በመዝመት ጠላቶችህን መውጋት የማልችለው ስለምንድን ነው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አንኩስን፥ “ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በአገልጋይህ ምን በደል አግኝተህብኛል?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አንኩስን፦ ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በባሪያህ ምን አግኝተህብኛል? አለው። |
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
አንተ ግን ከአገልጋይህ ጋር በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ገብታችኋልና ለአገልጋይህ በጎነትን አሳይ። እኔ በደለኛ ከሆንኩ፥ አንተው ራስህ ግደለኝ፤ ለምንስ ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ!”
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።
ዳዊትም፥ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያንጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አኪሽም፥ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት።