አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት።
1 ሳሙኤል 28:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም በቤቷ የሠባ ጥጃ ስለነበራት፥ ፈጥና ዐረደችው፤ ዱቄት ወስዳ ለወሰች፥ እርሾ የሌለው እንጀራም ጋገረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም በቤቷ የሠባ ጥጃ ስለ ነበራት፣ ፈጥና ዐረደችው፤ ዱቄት ወስዳ ለወሰች፣ ቂጣም ጋገረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም የሰባ ጥጃ ነበራት እሱንም በፍጥነት ዐረደች፤ ጥቂት ዱቄትም ወስዳ በማቡካት እርሾ ያልነካው ቂጣ ጋገረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሴቲቱም የሰባ ጥጃ በቤት ነበራት፤ ፈጥና አረደችው፤ ዱቄቱንም ወስዳ ለወሰችው፤ ቂጣም እንጀራ አድርጋ ጋገረችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሴቲቱም ማለፊያ እንቦሳ ነበራት፥ ፈጥና አረደችው፥ ዱቄቱንም ወስዳ ለወሰችው፥ ቂጣም እንጀራ አድርጋ ጋገረችው። |
አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት።