Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 15:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደኅና ስላገኘውም አባትህ የሰባውን ፍሪዳ አረደለት፤’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አገልጋዩም፣ ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በሰላም በጤና ስለ መጣም አባትህ የሠባውን ፍሪዳ ዐርዶለታል’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አገልጋዩም ‘ወንድምህ ተመልሶ ስለ መጣ ነው፤ አባትህ በደኅና ስላገኘው የሰባውን ወይፈን ዐርዶለታል’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እር​ሱም፦ ‘ወን​ድ​ምህ ከሄ​ደ​በት መጣ፤ አባ​ት​ህም የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረደ፤ በሕ​ይ​ወት አግ​ኝ​ቶ​ታ​ልና’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እርሱም፦ ወንድምህ መጥቶአልና በደኅና ስላገኘው አባትህ የሰባውን ፊሪዳ አረደለት አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 15:27
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌሎች ባርያዎችን ደግሞ ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ግብዣ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።


ከአገልጋዮቹም አንዱን ጠርቶ ‘ይህ ምንድነው?’ ብሎ ጠየቀ።


እርሱም ተቈጣ፤ ሊገባም አልፈለገም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው።


ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት፤’ አለው።


እርሱም ወደ እኔ መጥቶ በአጠገቤም ቆሞ ‘ወንድሜ ሳውል ሆይ! እይ፤’ አለኝ። እኔም ያን ጊዜውን ወደ እርሱ አየሁ።


ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፤ እጁንም ጭኖበት “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፤ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ፤” አለ።


ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባርያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም ሆነ በጌታ ዘንድ ከባርያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?


ሴትዮዋም በቤቷ የሠባ ጥጃ ስለነበራት፥ ፈጥና ዐረደችው፤ ዱቄት ወስዳ ለወሰች፥ እርሾ የሌለው እንጀራም ጋገረች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች