1 ሳሙኤል 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያንጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አኪሽም፥ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም፣ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያን ጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አንኩስም፣ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አንኩስን፥ “አሁን አገልጋይህ የሚያደርገውን ንገረው” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አንኩስን፦ አሁን ባሪያህ የሚያደርገውን ታያለህ አለው። አንኩስም ዳዊትን፦ እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ አለው። |
ሐና ግን አልሄደችም፤ ምክንያቱም ለባሏ፥ “ሕፃኑ ጡት እንደተወ፥ በጌታ ፊት ቀርቦ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም በዚያ እንዲኖር፥ አመጣዋለሁ” ብላው ነበርና ነው።
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።