Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 28:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አሁን አገ​ል​ጋ​ይህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ንገ​ረው” አለው። አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “እን​ግ​ዲህ በዘ​መኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዳዊትም፣ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያን ጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አንኩስም፣ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም፥ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያንጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አኪሽም፥ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም አንኩስን፦ አሁን ባሪያህ የሚያደርገውን ታያለህ አለው። አንኩስም ዳዊትን፦ እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 28:2
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤


ሐና ግን ከእ​ርሱ ጋር አል​ወ​ጣ​ችም። ለባ​ል​ዋም፥ “ሕፃ​ኑን ጡት እስከ አስ​ጥ​ለው፥ ከእ​ኔም ጋር እስ​ኪ​ወ​ጣና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስ​ኪ​ታይ ድረስ አል​ወ​ጣም፤ በዚ​ያም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብላ​ዋ​ለ​ችና።


እኔም ደግሞ ዕድ​ሜ​ውን ሙሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች በመቶ በመቶ፥ በሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ያልፉ ነበር፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከአ​ን​ኩስ ጋር በኋ​ለ​ኛው ጭፍራ በኩል ያልፉ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች