1 ሳሙኤል 27:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትና ተከታዮቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ሁለቱ ሚስቶቹ አብረው ነበሩ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው አሒኖዓምና የቀርሜሎሱ ተወላጅ ናባል አግብቶአት የነበረው አቢጌል ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነ ቤተ ሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ውስጥ ተቀመጡ፥ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቢግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ። |
የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።