Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 27:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዳዊትና ተከታዮቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ሁለቱ ሚስቶቹ አብረው ነበሩ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው አሒኖዓምና የቀርሜሎሱ ተወላጅ ናባል አግብቶአት የነበረው አቢጌል ነበሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከነ​ቤ​ተ​ሰቡ ከአ​ን​ኩስ ጋር በጌት ተቀ​መጡ፤ ከዳ​ዊ​ትም ጋር ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት አቤ​ግያ ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነ ቤተ ሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ውስጥ ተቀመጡ፥ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቢግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 27:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ዳዊት ተከታዮቹን ከነቤተሰባቸው ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ በኬብሮን ዙሪያ ባሉትም ታናናሽ ከተሞች ተቀመጡ።


ሳኦልም ዳዊት ወደ ጋት ሸሽቶ መሄዱን በሰማ ጊዜ እርሱን ፈልጎ ለማግኘት ያደርገው የነበረውን ሙከራ ሁሉ አቆመ።


ዳዊትና ተከታዮቹም እዚያ በደረሱ ጊዜ ከተማይቱ ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው መወሰዳቸውን ተረዱ፤


ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች የኢዝራኤላይቱን አሒኖዓምና የቀርሜሎሳይቱ የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌል ተማርከው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች