ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።
1 ሳሙኤል 23:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ናና፥ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ መስጠት የእኛ ድርሻ ነው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ና እንጂ፣ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እርሱን በምትፈልግበት ጊዜ ወደ እኛ ና፤ እኛም እርሱን ለአንተ ለንጉሡ አሳልፈን ለመስጠት ኀላፊነትን እንወስዳለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመውረድ ፈቃድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በንጉሡ እጅ ጥሎታልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ ንጉሥ ሆይ፥ ትወርድ ዘንድ ነፍስህ እንደ ወደደች ውረድ፥ በንጉሡም እጅ እርሱን አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን አሉት። |
ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።