Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዳዊትም፥ “የቅዒላ ነዋሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዳዊትም እንደ ገና፣ “የቅዒላ ገዦች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዳዊትም “የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎችስ ተከታዮቼንና እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡን ይሆን?” ሲል እንደገና ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዳዊ​ትም፥ “የቂ​አላ ሰዎች እኔ​ንና ሰዎ​ቼን በሳ​ኦል እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ና​ልን?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዳዊትም፦ የቅዒላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን? አለ። እግዚአብሔርም፦ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ብሎ ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 23:12
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።


አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ናና፥ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ መስጠት የእኛ ድርሻ ነው” አሉት።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!


ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፥ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፥ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፥ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ ነው” አለ።


በሰው ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።


የይሁዳም ሰዎች፥ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልና ስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው።


የቅዒላ ሰዎች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባርያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ለአገልጋይህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” ጌታም፥ “አዎን ይወርዳል” አለው።


ጌታም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፤ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።


አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን አሰማኝ፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳውቀኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች