1 ሳሙኤል 21:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል፥ እነሆ፥ ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም፣ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል ከፈለግህ ውሰደው፤ ከርሱ በቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም “በኤላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በእኔ ዘንድ አለ፤ እርሱም ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅሎ ተቀምጦአል፤ የምትፈልገው ከሆነ ውሰደው፤ በዚህ የሚገኝ የጦር መሣሪያ እርሱ ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም “እርሱኑ ስጠኝ! ከእርሱ የተሻለ ሰይፍ የትም አይገኝም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም፦ በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ፥ እነሆ፥ በመጎናጸፊያ ተጠቅልሎ ከዚህ ከኤፉዱ በኋላ አለ፥ ትወድደውም እንደ ሆነ ውሰደው፥ ሌላ ከዚህ የለም አለ። ዳዊትም፦ እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱን ስጠኝ አለው። |
ዳዊት አቢሜሌክን፥ “የንጉሡ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ፥ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው።
ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቢሜሌክ ጌታን ጠይቆለታል፤ ለዳዊትም ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ።