1 ሳሙኤል 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ዳዊት አቢሜሌክን፥ “የንጉሡ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ፥ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ዳዊት አቢሜሌክን፣ “የንጉሡ ጕዳይ ስላስቸኰለኝ፣ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ዳዊትም አቤሜሌክን “የምትሰጠኝ ጦር ወይም ሰይፍ በአንተ ዘንድ ይገኛልን? የንጉሡ ትእዛዝ አስቸኳይ ስለ ሆነ ጦሬንም ሆነ ሌላውንም መሣሪያዬን ለመያዝ ጊዜ አላገኘሁም ነበር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ዳዊትም አቤሜሌክን፥ “የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኰለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እንዳለ እይልኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ዳዊትም አቢሜሌክን፦ የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አለ ወይ? አለው። ምዕራፉን ተመልከት |