1 ሳሙኤል 20:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ ጠዋት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፥ ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፣ ከዳዊት ጋራ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት በቀጠሮአቸው መሠረት ዮናታን ዳዊትን ለማግኘት ወደ ሜዳ ሄደ፤ ሲሄድም አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፥ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። |